Welcome to North Shoa Zone Administrative Office

  • Increase font size
  • Default font size
  • Decrease font size
Welcome to North Shoa Zone Administrative Office

ሀይለማርያም ማሞ ትምህርት ቤት የአልማዝ እዮቤልዩ በዓሉን አከበረ

E-mail Print PDF

Image may contain: 13 people, people sitting and outdoor

ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማሩን ሂደት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደ የሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፎ እንደሚያስፈልገው ተገለፀ፡፡
በደብረ ብርሀን ከተማ የሚገኘው የሀይለማርያም ማሞ ትምህርት ቤት የአልማዝ እዮቤልዩ በዓሉን ከሚያዚያ 27 2009 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 3ቀናት ባከበረበት ወቅት ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማዘመን በሚያደርገው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ላይ የትምህርት ቤቱ የቀድሞ ተማሪዎችም ሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልገው አስታወቀ፡፡
በእለቱ የክብር እንግዳ የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን

 

Read more...
 

የአማራ ክልል የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኮሚሽን ኮሚሽነር የስራ ጉብኝት አደረጉ

E-mail Print PDF

የአማራ ክልል የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት ዶ/ር በላይነህ አየለ እና የቀድሞው የአብክመ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ብነግረው ዋሌ በጋራ በሰሜንሸዋ ዞን አስተዳደር በመገኘት ከአመራሮች ና ከኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዋና የሥራ ሂደት ሠራተኞች ጋር በመገናኝት የትውውቅ ፕሮግራም ጋደረጉ በኋላ በቀሪ ወራቶች በፕላዝማ ችሎት እና በኢንተር ፕራይዝ የሚደራጁ ቀበሌዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው ለወጣቱ የስራ እድል በመፍጠር ስራዎች እንዲሰሩና በተጨማሪም በ2009 የበጀት አመት በአዲስ መንፈስ በመነሳት መቀጠል ያለባቸውን እንዲሁም ለተቋሙ ቢስተካከሉ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣሉ በተባሉ ጉዳዮች ላይ ከቤቱ የተነሱ አስተያየቶች ለምሳሌ የክልሉ ኮር አመራሮች ለተቋሙ ልዩ ትኩረት በመስጠት በበጀት እና በሰው ኃይል እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ እንዲደግፍ ቢደረግ የሚል አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ኮሚሽነሩም በተቻለ አቅም ሁሉ ተቋሙን ሊያሰራ የሚችል ቅርፅ የሚይዝበትን እንደሚያደርጉና የክልሉ አመራሮችም ድጋፋቸውን በሙሉ ፈቃደኝነት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡ በዞኑ በኩልም የቀድሞው የኤጀንሲው ስራ አስኪያጅ አቶ ብነግረው ዋሌ ስራዎች ከዜሮ እንዳይጀምሩ አብረው በመገኘት ኮሚሽኑ ለውጥ እንዲያመጣ በጋራ በመተጋገዝ ያደረጉት ድጋፍ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ሲሆን ሌሎችም ከዚህ መማር እንዳለባቸው የሚያሳይ መሆኑን አስተያየት ተሰጥቷል!!

ANRS Northshoa Zone AdministrationANRS STCT Commision

Last Updated on Friday, 27 May 2016 12:43
 

በሰሜን ሸዋ ዞን ደ/ብርሃን ከተማ ሲካሄድ የነበረው የቪዲዬ ኮንፈረንስ ስልጠና ተጠናቀቀ!

E-mail Print PDF

በትምህርት ዘርፍ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድርና ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ተናገሩ:: በክልሉ በሁልም ዞኖች በሚካሄደው የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና ወቅት በትምህርት ዘርፍ የ2ኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽ እቅድ ውይይት ላይ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ በትምህርት ዘርፍ ያለው የመልካም አስተዳደር ችግር እቅዱን ለማሳካት ተግዳሮት ይሆናል በሚል ከሰልጣኖች በቀረበው ጥያቄ መሰረት የክልሉ ምዕ/ርዕሰ መስተዳድር ችግሩ መኖሩን ገልፀው፡፡
በአጠቃላይ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መነሻቸው 3 መሆናቸውን ጠቁመው በተለይ በትምህርት ዘርፍ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር በትምህርት ጥራታችን ላይ ጥላሸት እንዳይጥልበት ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል፡፡
በክልል ደረጃ ከትምህርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈታ እቅድ በክልል ደረጃ መዘጋጀቱን የተናገሩት ም/ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ በመምህራን፣ በትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች የሚነሱ የጥቅማጥቅም ጉዳዮች በትምህርት ስርአቱ አንዱ የመልካም አስተዳደር ችግር በመሆኑ በቀጣይ ቢሮው ዋና ተግባር አድርጎ በመስራት አግባብነት ያላቸውን የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ የአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚፈቅደውን ያህል መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን አቶ ብናልፍ አንዷለም ገልፀዋል፡፡


ምንጭ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን


Last Updated on Wednesday, 24 February 2016 11:17
 

የአብክመ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኤጀንሲ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና አውደ-ጥናት እያካሄደ ነው

E-mail Print PDF

የአብክመ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኤጀንሲ የ2008 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና አውደ-ጥናት ከየካቲት 16-18/2008 ዓ.ም. በዞናችን ከተማ በደብረ ብርሃን በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በስብሰባው ላይ ከዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ትውውቅበተጨማሪ የተለያዩ መመሪያዎችና ፖሊሲዎች ትውውቅ እንዲሁም አዳዲስ አሰራሮች ማለትም አዲስ የተለሙ ሶፍትዌሮችና ሲስተሞች ትውውቅ እንደሚደረግ የኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብነግረው ዋሌ ተናገረዋል፡፡ በአወውደ-ጥናቱ ላይ የምስራቅ አማራ ዞኖች የሚሳተፉ ሲሆን የምዕራብ አማራ ዞኖች ቀደም ሲል በዳንግላ ከተማ መሳተፋቸው ይታወቃል፡፡

Last Updated on Wednesday, 24 February 2016 11:28
 

በደብረ ብርሃን ለሁለት ሳምንታት የሚቆየው የንግድ ትርኢትና ባዛር በደማቅ ስነ-ስርዓት ተከፈተ

E-mail Print PDF

ከ16/05/08 እስከ 28/05/2008 ዓ.ም የሚቆየው የእድገት ብርሃን በደብረ ብርሃን የንግድ ትርኢት ና ባዛር በዞኑ ህዝቦች፣ ከተለያዩ አካባቢ በመጡ እንግዶች እና ከፈረንሳይ እህት ከተማ ብሉሚኒል ከመጡ የክብር እንግዶች ጋር በታላቅ ድምቀት የተከፈተ ሲሆን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ግርማ የሺጥላ እንዲህ ሲሉ ተደምጠዋል በዚህ ዕለት በታላቅ ዝግጅት እና ሰፊ ንቅናቄ የተከፈተው በዓል እስከ መጨረሻው ቆይታ የተሳካ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ ሁል ጊዜ ለቴክኖሎጂና ለተለያዩ አዳዲስ ምርትና አገልግሎት ለመቀበል ና ለመሸጥ እንዲሁም ለገበያ ትስስር ቅርብ የሆነው ህዝባችን ዛሬም ሰፊ ርብርብ በማድረግ የልማት አጋር መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ፡፡ በተጨማሪም የ2ኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እድ ዘመን በተሸለ ሁኔታ ለማስቀጠል ከህዝባችን ጋር የምንሰራቸው ሰፊ ስራዎች በቀጣይም ይኖሩናል ከልማት ስራዎቻችን ፍጥነትና ተደራሽነት እንዲሁም ጥራት ማረጋገጥ ጎን ለጎን በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀን ወደ ንቅናቄ ተገብቷል ካሉ በኋላ በዚህ ባዛር ዝግጅት ወቅት ጉልህ ድርሻ ላላቸው አካላቶች በህዝቡና በዞን አስተዳደር ስም ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Last Updated on Wednesday, 24 February 2016 09:04
 

Advertise Here

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5
mod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_counter
mod_vvisit_counterToday3
mod_vvisit_counterYesterday4
mod_vvisit_counterThis week23
mod_vvisit_counterLast week44
mod_vvisit_counterThis month91
mod_vvisit_counterLast month147
mod_vvisit_counterAll days26555

We have: 2 guests online
Your IP: : 54.162.181.75
 , 
Today: September 21, 2017

Calendar

September 2017
SMTWTFS
12
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930

Feedback

Tell us About Our Service